ብቁ ነዎት?

የተሻለ እንግሊዝኛ

የተሻለ ሕይወት


ነጻ የእንግሊዝኛ ትምህርት ለአዲስ መጤዎች


ስለ  በአዋቂ ስደተኞች የእንግሊዝኛ ፕሮግራም (Adult Migrant English Program) 

 • እስከ 510 ስዓታት የሚደርስ የእንግሊዝኛ ትምህርት እና ነጻ የሕጻን ክብካቤን ያግኙ (ብቁ ከሆኑ የሚሰጥ)።
 • በአውስትራሊያ ውስጥ ለመኖር፣ ሥራ ለመሥራት እና ትምህርት ለመማር የሚጠቅም ተግባራዊ እንግሊዝኛ ትምህርት ይማሩ።
 • የመንግንሥት እና የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ይማሩ።
 • ልክ እንደ እርስዎ ገና ወደ አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጡ አዳዲስ ጓደኞችን ያግኙ።
 • ራስዎን ለሥራ ወይም ለከፍተኛ ትምህርት ያዘጋጁ እና መፃዒ ሕይወትዎ እንዴት እንደሚሆን ከወዲሁ ዕቅድ ያውጡ።

 

ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች 

 • ወደ አውስትራሊያ ለመግባት የሚያስችል ትክክለኛ የስደተኛ ቪዛ ተሰጥቶታል። የቪዛው ደብዳቤ በደረስዎት በስድስት ወራት ውስጥ እባክዎ ለፕሮግራሙ ይመዝገቡ።
 • የቤተሰብ፣ የባለሙያነት፣ የሰብዓዊነት፣ የጋብቻ ወይም በሌላ መልኩ የተፈቀደ ጊዜያዊ ቪዛ አልዎት።*
 • በእንግሊዝኛ መናገር/ማንበብ/መጻፍ አይችሉም ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎችን ማሻሻል ይፈልጋሉ።
 • ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በላይ ነው። ዕድሜያቸው ከ 15 እስከ 17 የሚሆን አንዳንድ ታዳጊ ወጣት ስደተኞችም ብቁ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል።

*የተፈቀዱ ጊዜያዊ ቪዛዎች የሥራ እና የዕረፍት ቪዛን፣ የሥራ የዕረፍት ቪዛ ወይም የጎብኚ ቪዛዎችን እንደማያካትቱ እባክዎ ልብ ይበሉ።

 

እንደ አስፈላጊነቱ ሊስተካከል የሚችል የመማር አማራጭ 

 • በመላ ኲዊንስላንድ በሚገኙ መማሪያ ማእከላት ውስጥ በሙሉ ጊዜ ወይም በትርፍ ጊዜዎ ይማሩ።
 • ሙሉ ጊዜ ሰጥተው መማር የማይችሉ ከሆነ በበጎ ፈቃደኛ የቤት ውስጥ አስተማሪ ድጋፍ ያግኙ።
 • በርቀት ትምህርት በኩል በመስመር ላይ (በኢንተርኔት) ይማሩ።
 • አውስትራሊያ በደረሱ በአምስት ዓመታት ውስጥ የእርስዎን የ AMEP ትምህርት ያጠናቅቁ።

 

በመማሪያ ክፍል ውስጥ ምን እማራለሁ?

 • ከእርስዎ የእንግሊዝኛ ችሎታ ጋር በሚመጣጠን መማሪያ ክፍል ውስጥ ገብተው ይማሩ።
 • ትምህርቱን በሚማሩበት ጊዜ በማኅበረሰብ ጉዳይ አስፈጻሚ ሹሞች እና በእርስዎ የ AMEP ኬዝ ማናጀር አማካይነት ድጋፍ ያግኙ።
 • ስለ የአውስትራሊያ የሥራ ቦታ ቋንቋ፣ ባሕል እንዲሁም ልማድና ትውፊቶች ይማሩ።
 • በእርስዎ የመማር ችሎታ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ከዚህ ቀደም ውስን የሆነ የትምህርት ዕድል ከነበርዎት ተጨማሪ የእንግሊዝኛ ትምህርት በግል አስጠኚ አማካይነት ይማሩ።
 • እርስዎ እንግሊዝኛ በሚማሩበት ጊዜ ለልጅዎ ነጻ የሕፃን ክብካቤ ያግኙ (ብቁ ከሆኑ ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት)።
 • ለሥራ ቃለ መጠይቆች ራስዎን ያዘጋጁ እና ራስዎን የሚገልጽ አጭር ማመልከቻ (ሬዝዩሜ) ይጻፉ።
 • እስከ 80 የሥራ ሰዓታት የሚታሰብ የሥራ ልምድ ያግኙ።

 

ብሮሹር ያውርዱ

እንዴት መመዝገብ እችላለሁ

 

Step 1

አሁን ይጠይቁ

ወይም

በስልክ ቁጥር፦ (07) 3244 5488

ወይም

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የ TAFE Queensland ቢሮን ያነጋግሩ።
 ይህን ሲያደርጉ እባክዎ የእርስዎን ፓስፖርት እና ቪዛ መረጃዎች ዝግጁ አድርገው ይቅረቡ።

እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ
Step 2

በ AMEP ኬዝ ማናጀር አማካኝነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ፈተናን ይፈተኑ።
Step 3

የእርስዎ የ AMEP ኬዝ ማናጀር ወደ አንድ መማሪያ ክፍል ይመድብዎታል።

ስለ የእኛ የእንግሊዝኛ ትምህርቶች አሁን ጥያቄዎችን ይጠይቁ